ማቴዎስ 12:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ አንዳንድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ! አንተ ተአምር ስታደርግ ማየት እንፈልጋለን!” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አንዳንድ ፈሪሳውያንና የአይሁድ ሃይማኖት መምህራን፣ “መምህር ሆይ፤ ከአንተ ምልክት ማየት እንፈልጋለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና “መምህር ሆይ! ከአንተ ምልክት ማየት እንፈልጋለን” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና “መምህር ሆይ! ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን፤” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና፦ መምህር ሆይ፥ ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን አሉ። |
ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጥተው በተሰበሰቡ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክት ለማየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።