La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 10:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” ሲል ጠየቀው። ዕውሩም ሰው፥ “መምህር ሆይ፥ እባክህ ዐይኔ እንዲያይ አድርግልኝ፤” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው። ዐይነ ስውሩም፣ “መምህር ሆይ፤ ዳግም እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም፥ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው። ዐይነ ስውሩም፥ “መምህር ሆይ፤ እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢየሱስም መልሶ “ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?” አለው። ዕውሩም “መምህር ሆይ! አይ ዘንድ፤” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም መልሶ፦ ምን ላደርግልህ ትወዳለህ? አለው። ዕውሩም፦ መምህር ሆይ፥ አይ ዘንድ አለው።

Ver Capítulo



ማርቆስ 10:51
11 Referencias Cruzadas  

በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ለሰሎሞን ተገልጦ “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” ሲል ጠየቀው።


በየአደባባዩም ሰው ሁሉ እጅ እንዲነሣቸውና ‘መምህር ሆይ!’ ብሎ እንዲጠራቸው ይፈልጋሉ፤


እናንተ ግን መምህራችሁ አንድ ብቻ ስለ ሆነና ሁላችሁም ወንድማማቾች ስለ ሆናችሁ፥ ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ።


እናንተ ግን፥ አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ገና ሳትለምኑት አስቀድሞ ስለሚያውቅ እንደ እነርሱ አትሁኑ።


“ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤


እርሱም “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው።


እርሱም ሸማውን ጣለና ዘሎ ተነሥቶ ወደ ኢየሱስ ሄደ።


ኢየሱስም “ማርያም!” አላት። እርስዋም ወደ እርሱ ዞር ብላ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ረቡኒ!” አለችው፤ ትርጓሜውም “መምህር ሆይ!” ማለት ነው።


አዛዡም የልጁን እጅ ይዞ ገለል አደረገውና “የምትነግረኝ ነገር ምንድን ነው?” ሲል ለብቻው ጠየቀው።


ስለዚህ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፥ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ።