ሉቃስ 18:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህች መበለት ስለ ነዘነዘችኝ እፈርድላታለሁ፤ አለበለዚያ ግን ዘወትር እየተመላለሰች ታሰለቸኛለች።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህች መበለት ስለምትጨቀጭቀኝ እፈርድላታለሁ፤ አለዚያ ዘወትር እየተመላለሰች ታሰለቸኛለች።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህች መበለት ስለምታደክመኝ፥ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ፤’ አለ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህቺ ሴት እንዳትዘበዝበኝ፥ ዘወትርም እየመጣች እንዳታታክተኝ እፈርድላታለሁ’።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። |
እርሱ ግን አንድም ቃል ሳይመልስላት ዝም አለ፤ በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፥ “ይህች ሴት እየተከተለችን ስለምትጮኽ እባክህ አሰናብታት!” ሲሉ ለመኑት።
ቀድመው እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት ሰዎች፦ “ዝም በል!” ብለው ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን በይበልጥ ከፍ አድርጎ፦ “የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ!” ይል ነበር።