ኢያሱ 8:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ ቀደም ብሎ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እስራኤላውያን ሁሉና መጻተኞች ሽማግሌዎቻቸው፥ ሹሞቻቸውና ዳኞቻቸው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከተሸከሙት ከሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት ግራና ቀኝ እኩሌቶቹ ከጌሪዚም ተራራ ፊት ለፊት፥ እኩሌቶቹ ደግሞ ከኤባል ተራራ ፊት ለፊት ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል በሙሉ መጻተኛውም ሆነ ተወላጁ፣ ሽማግሌዎቻቸውም ሆኑ ሹማምታቸው እንዲሁም ዳኞቻቸው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ተሸከሙት ሌዋውያን ካህናት ፊታቸውን አዙረው፣ በታቦቱ ግራና ቀኝ ቆመው ነበር። የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ መመሪያ በሰጠ ጊዜ፣ አስቀድሞ ባዘዘው መሠረት፣ ግማሹ ሕዝብ በገሪዛን ተራራ፣ ግማሹ ደግሞ በጌባል ተራራ ፊት ለፊት ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ እንዲባረኩ የጌታ ባርያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የአገሩ ተወላጆችም፥ መጻተኞችም፥ እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ለፊት ሆነው፥ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ ይባርኩአቸው ዘንድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ ጸሓፊዎቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የሀገሩ ልጆችም፥ መጻተኞችም እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ አጠገብ፥ እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ አጠገብ ሆነው፥ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በግራና በቀኝ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ ይባርኩ ዘንድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የአገሩ ልጆችም፥ መጻተኞችም፥ እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ሆነው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። |
ይህም ሕግ ለሁላችሁም ማለትም ለእናንተ ለእስራኤላውያንም ሆነ፥ በእናንተ መካከል ለሚኖሩት መጻተኞች ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ እነዚህን የሥርዓት መመሪያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ እናንተም ሆናችሁ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ናችሁ።
ሁሉም ሰምተውት አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት እንዲማሩና የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ በጥንቃቄ እንዲጠብቁ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም፥ ልጆችንም፥ በከተሞቻችሁ የሚኖሩ መጻተኞችንም በአንድነት ሰብስቡ።
ከዚያ በኋላ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አገልጋዮች ለሆኑት ለሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሕዝብ አለቆች ሰጣቸው።
ስለዚህም እርሱ መላውን እስራኤልን፥ ሽማግሌዎችን፥ መሪዎችን፥ ዳኞችንና የጦር አዛዦችን በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ እኔ በዕድሜ ሸምግያለሁ፤
ኢያሱ የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ በሴኬም በአንድነት ሰበሰበ፤ ሽማግሌዎችን፥ አለቆቻቸውን፥ ዳኞችንና የእስራኤልን የጦር አዛዦች ሁሉ ጠራ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ፤
የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጡ፦ “የሌዊ ዘር የሆኑት ካህናት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ሲነሡ በምታዩበት ጊዜ፥ ሰፈሩን ለቃችሁ እነርሱን ተከተሉ።
ለሕዝቡ እንዲነግር እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ሁሉ ነገር እስኪፈጸም ድረስ ካህናቱ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል እንደ ቆሙ ቈዩ፤ ሙሴም ኢያሱን ያዘዘው ይህንኑ ነበር፤ ሕዝቡም ፈጥኖ ወንዙን ተሻገሩ።
የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ወጥተው እግሮቻቸው ደረቁን መሬት በረገጡ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ ወደ ቦታው ተመልሶ እንደ ቀድሞው ሞልቶ ይፈስ ጀመር።