‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ዮሐንስ 4:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ለማታውቁት አምላክ ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን መዳን የሚመጣው ከአይሁድ ስለ ሆነ ለምናውቀው አምላክ እንሰግዳለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ሳምራውያን ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን ድነት ከአይሁድ ስለ ሆነ ለምናውቀው እንሰግዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ለምናውቀው እንሰግዳለን፥ መዳን ከአይሁድ ነውና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ ግን ለምናውቀው እንሰግዳለን፤ መድኀኒት ከአይሁድ ወገን ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን። |
‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።
ወደ ዘሩባቤልና ወደ ጐሣ መሪዎችም ቀርበው “ቤተ መቅደሱን ከእናንተ ጋር አብረን እንሥራ፤ ይህንኑ እናንተ የምታመልኩትን እግዚአብሔር እኛም እናመልከዋለን፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት አስራዶን ወደዚህ አገር ከላከንም ጊዜ ጀምሮ መሥዋዕት ስናቀርብለት ቈይተናል” አሉአቸው።
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።
ስለዚህ ብዙ ሕዝቦች እንዲህ ይላሉ፦ “ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ስለሚገኝ ኑ ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤተ መቅደስም እንሂድ፤ እርሱ ፈቃዱን እንድናደርግ ያስተምረናል፤ እኛም በእርሱ መንገድ እንሄዳለን።”
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
በከተማችሁ እየተዘዋወርኩ የአምልኮ ስፍራዎቻችሁን ስመለከት ‘ለማይታወቅ አምላክ’ ተብሎ የተጻፈበትን የመሠዊያ ቦታ አገኘሁ፤ እንግዲህ እኔ አሁን የምነግራችሁ ስለዚሁ ሳታውቁ ስለምታመልኩት አምላክ ነው።
እንግዲህ ሰዎች በቀድሞ ዘመን ባለማወቅ ያደረጉትን እግዚአብሔር ችላ ብሎ አልፎታል፤ አሁን ግን በየአገሩ ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ አዞአል፤
ስለዚህ እግዚአብሔር ልጁን የላከው በመጀመሪያ ለእናንተ ነበር፤ ይህንንም ያደረገው እያንዳንዳችሁን ከክፉ መንገዳችሁ በመመለስ እንዲባርካችሁ ነው።”
እናንተ አሕዛብ እንደ ቅርንጫፍ ተቈርጠው በወደቁት አይሁድ ላይ አትታበዩ፤ ብትታበዩ ግን እናንተ ቅርንጫፎች ብቻ በመሆናችሁ ሥሩ እናንተን ይሸከማችኋል እንጂ እናንተ ሥሩን የማትሸከሙ መሆናችሁን አስታውሱ።