ኢዮብ 18:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለምን አንተ እኛን እንደ እንስሶች ትቈጥረናለህ? ለምንስ እንደ ደንቆሮዎች የማናስተውል አድርገህ ትመለከተናለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለምን እንደ ከብት መንጋ እንቈጠራለን? እንደ ደንቈሮስ ለምን ታየናለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ምንስ እንደ እንስሶች ተቈጠርን? ስለ ምንስ በዓይንህ ፊት ቀለልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ምንስ እንደ እንስሳ በፊትህ ዝም አልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምንስ እንደ እንስሶች ተቈጠርን? ስለ ምንስ በዓይንህ ፊት ረከስን? |