ኤርምያስ 18:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም እዚያ ሄጄ ሸክላ ሠሪው በመንኰራኲሩ ላይ ሲሠራ አየሁት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድሁ፤ ሸክላውንም በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ሸክላ ሠሪው ቤትም ወረድሁ፥ እነሆም፥ ሥራውን በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሸክላ ሠሪውም ቤት ወረድሁ፤ እነሆም ሥራውን በዓለት ላይ ሲሠራ አገኘሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሸክላ ሠሪው ቤትም ወረድሁ፥ እነሆም፥ ሥራውን በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር። |
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር።