ያዕቆብ 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰላም ወዳድ ሰዎች ሰላምን ዘርተው የጽድቅን ፍሬ ይሰበስባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል። |
እኔም ‘እንግዲህ ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤ ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፤ የማይለዋወጥ ፍቅርን ሰብስቡ፤ እነሆ ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ የምትመለሱበት ጊዜ አሁን ነው! እኔም መጥቼ ፍትሕን አሰፍንላችኋለሁ’ አልኩ።
ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።