ኢሳይያስ 22:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊትን ቤት የቊልፍ መክፈቻ እሰጠዋለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን መዝጋት፥ የሚዘጋውንም መክፈት የሚችል አይኖርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊትን ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትንም ክብር እሰጠዋለሁ፤ ይገዛል፤ በአገዛዝም የሚበልጠው የለም። የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ይከፍታል፤ የሚዘጋም የለም፤ እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፥ እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም፥ እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም። |
ለዚህም ኢሳይያስ ሲመልስ እንዲህ አለ “እናንተ የንጉሥ ዳዊት ቤተሰብ ሆይ! ስሙ፤ ሰውን ማሰልቸታችሁ አንሶ እግዚአብሔርንስ ማሳዘን ትፈልጋላችሁን?
ሶርያ ከእስራኤል መንግሥት ጋር በመተባበር የጦር ቃል ኪዳን መግባትዋን የይሁዳ ንጉሥ በሰማ ጊዜ እርሱና ሕዝቡ ደንግጠው ልባቸው በነፋስ እንደ ተመታ ዛፍ ተናወጠ።
እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።
“ለፊላደልፍያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ቅዱስና እውነተኛ ከሆነው፥ የዳዊት ቤት ቊልፍ ከያዘው የተነገረ ነው፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋውም፤ እርሱ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍተውም።