ሆሴዕ 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ራሳቸው ጣዖት አምላኪዎች ስለ ሆኑ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልተገኙም። ልጆቻቸውም እንደ ጣዖት ልጆች ተቆጥረዋል፤ ስለዚህ በዚህ ወር መባቻ እነርሱም ምድራቸውም አብረው ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም፤ ዲቃሎች ወልደዋልና፤ ስለዚህ የወር መባቻ በዓላቸው፤ እነርሱንና ዕርሻቸውን ያጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና ጌታን አታልለዋል፤ አሁን ደግሞ እነርሱን ከርስታቸው ጋር የወሩ መባቻ ይበላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ከድተዋል፤ አሁንም ኵብኵባ እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ወንጅለዋል፥ አሁንም አንድ ወር እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል። |
እኔ የምናገረውን አትሰሙም፤ ለማወቅም አትፈልጉም፤ ከጥንት ጀምሮ ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው፤ ይህም የሆነው እናንተ በጣም ከዳተኞች መሆናችሁንና ከተወለዳችሁ ጀምሮ ዐመፀኞች ተብላችሁ መጠራታችሁን ዐውቃለሁ።
በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት በማጓደል ዐምፀናል፤ አምላካችንን ትተን ወደ ኋላ አፈግፍገናል፤ በልባችን ውስጥ ውሸትን አውጠንጥነን ስም በማጥፋትና በከሐዲነት ገልጠናቸዋል።
ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የምላቸውን ንገራቸው፤ እኔ የተናገርኩት ሁሉ ይፈጸማል፤ ከቶም አይዘገይም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።”
“ከእኔ ርቀው ስለ ሄዱ ወዮላቸው! በእኔም ላይ ስለ ዐመፁ ጥፋት ይምጣባቸው፤ እኔ ልታደጋቸው ፈልጌ ነበር፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።