ዕብራውያን 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ክርስቶስ የካህናት አለቃ የመሆንን ክብር በገዛ ራሱ አልወሰደም፤ ነገር ግን እርሱ የካህናት አለቃ የመሆንን ክብር ያገኘው፥ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ካለው ከእግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ክርስቶስ ሊቀ ካህናት የመሆንን ክብር ለራሱ አልወሰደም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር፣ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም፤ ነገር ግን “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤” ያለው እርሱ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ ክርስቶስም ሊቀ ካህናት ይሆን ዘንድ ራሱን ያከበረ አይደለም፤ ነገር ግን፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለድሁህ” ያለው እርሱ ራሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም ነገር ግን፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው፤ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በኤፍራታ ምድር የምትገኚ ቤተልሔም ሆይ! ከይሁዳ ትናንሽ ከተሞች አንድ ብትሆኚም እንኳ ከአንቺ አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ የእስራኤልን ሕዝብ የሚመራ ገዢ ይወጣልኛል።”
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ዋጋ አይኖረውም እኔን የሚያከብረኝ አባቴ ነው፤ እርሱም ‘እናንተ አምላካችን’ የምትሉት ነው።
እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት በማስነሣቱ ይህንኑ ተስፋ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞታል፤ ይህም በሁለተኛው መዝሙር፥ ‘አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤’ ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።
እግዚአብሔር ከቶ ከመላእክት መካከል፥ “አንተ ልጄ ነህ፤ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤” ወይም “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ማንን ነው?
ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ።