የልያ አገልጋይ ዚልፋ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት።
የልያ አገልጋይ ዘለፋም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤
የልያ ባርያ ዘለፋም ወንድ ልጅን ለያዕቆብ ወለደች።
የልያ አገልጋይ ዘለፋም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች።
የልያ ባሪያ ዘለፋም ወንድ ልጅን ለያዕቆብ ወለደች።
ልያም “እንዴት የታደልኩ ነኝ!” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው።
ልያም መውለድ እንዳቆመች በተገነዘበች ጊዜ አገልጋይዋን ዚልፋን እንደ ሚስት አድርጋ ለያዕቆብ ሰጠችው፤
የልያ አገልጋይ የነበረችው የዚልፋ ልጆች ጋድና አሴር ናቸው። እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በመስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ናቸው።
ጋድ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከዛብሎን ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል።
ከጋድ ነገድ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ የተቈጠሩት፤
የሮቤልና የጋድ ነገዶች እጅግ ብዙ የከብት መንጋ ነበራቸው፤ የያዕዜርና የገለዓድ ምድር ለከብት ተስማሚ መሆኑን ባዩ ጊዜ፥