ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በኬብሮን የመምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች ወደአሉበት ስፍራ ለመኖር ሄደ፤ እዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።
ዘፍጥረት 26:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጒድጓድ ቈፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ፤ ድንኳንም ተከለ፤ አገልጋዮቹም በዚያ የውሃ ጕድጓድ ቈፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም መሠዊያን ሠራ የጌታንም ስም ጠራ፥ በዚያም ድንኳን ተከለ፥ የይስሐቅም አገልጋዮች በዚያ ጉድጓድ ማሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ፤ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፤ በዚያም ድንኳን ተከለ፤ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም መሠዊያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፥ በዚይም ድንኳን ተከለ፤ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ። |
ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በኬብሮን የመምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች ወደአሉበት ስፍራ ለመኖር ሄደ፤ እዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።
እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሠዊያው ላይ አጋደመው።
እግዚአብሔር ያዕቆብን “አሁን ተነሥተህ ወደ ቤትኤል ሂድና እዚያ ኑር፤ በዚያም ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድክ ጊዜ ለተገለጥኩልህ አምላክ ለእኔ መሠዊያ ሥራ” አለው።
ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዐይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው።