ዘፀአት 27:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርሱም መደገፊያ ኻያ የነሐስ እግሮች ያላቸው ኻያ ምሰሶዎች ሥራ፤ በእነርሱም ላይ ከብር የተሠሩ ዘንጎችና ኩላቦች ይኑሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሃያ ምሰሶዎች፣ ሃያ የንሓስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ይኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከናስ የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ እግሮች ይሁኑለት፤ የምሰሶዎቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከናስ የተሠሩ ሀያ ምሰሶችና ሀያ እግሮች ይሁኑለት፤ የምሶሶቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ። |
ለዚህም መጋረጃ ኩላቦች ያሉአቸው አምስት ምሰሶዎችን ሠሩ፤ የእነርሱንም ጒልላቶችና ዘንጎቹን በወርቅ ለበጡ፤ ለምሰሶዎቹም ማቆሚያ አምስት የነሐስ እግሮች ሠሩ።
በዙሪያ ያለው የአደባባይ አጥርና ወደ አደባባዩ የሚያስገባው ደጃፍ የሚቆሙባቸውን እግሮች፥ እንዲሁም የድንኳኑና በዙሪያው ያለውን የአደባባይ አጥር ካስማዎችን ሁሉ ሠራ።
ሁለቱ ዐምዶች አንድ ዐይነት ቅርጽ ያላቸው ሆነው እያንዳንዳቸው ስምንት ሜትር ቁመትና አምስት ሜትር የሚያኽል ዙሪያ ነበራቸው፤ ውስጣቸውም ክፍት ነበር፤ ብረቱም ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ውፍረት ነበረው፤