“የእስራኤል ሕዝብ በሐዘን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኛ እንዳልተገራ ወይፈን ነበርን፤ አንተ ግን መታዘዝን አስተማርከን፤ አንተ አምላካችን ስለ ሆንክ አሁንም ወደ አንተ ወደ አምላካችን መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን።
ዘዳግም 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ አስከሬኑ ወድቆ ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ ሆና የምትገኘው ከተማ መሪዎች ለሥራ ያልደረሰች፥ በጫንቃዋም ላይ ቀንበር ያልተጫነባት አንዲት ጊደር ይምረጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይዘው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይውሰዱ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለተገደለውም ሰው አቅራቢያ የሆነች የከተማዪቱ ሽማግሌዎች ከላሞች ለሥራ ያልደረሰችውን፥ ቀንበርም ያልተጫነባትን ጊደር ይውሰዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ተገደለውም ሰው አቅራቢያ የሆነችው የከተማይቱ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችውን ቀንበርም ያልተጫነባትን ጊደር ይውሰዱ፤ |
“የእስራኤል ሕዝብ በሐዘን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኛ እንዳልተገራ ወይፈን ነበርን፤ አንተ ግን መታዘዝን አስተማርከን፤ አንተ አምላካችን ስለ ሆንክ አሁንም ወደ አንተ ወደ አምላካችን መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን።
“ይህ እኔ ያዘዝኩት የሕጉ ሥርዓት ነው፦ ነውር የሌለባትና በጫንቃዋ ላይ ቀንበር ተጭኖባት የማታውቅ አንዲት ቀይ ጊደር እንዲያመጡ ለእስራኤላውያን ንገሩአቸው።
በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።
በዚያን ጊዜ መሪዎችህና ዳኞችህ ሄደው አስከሬኑ ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ አንሥተው ባቅራቢያ እስከምትገኘው እስከያንዳንዱ ከተማ ድረስ ርቀቱን ይለኩት፤
እርስዋንም ጨርሶ ወዳልታረሰና ምንም ተክል ወዳልተተከለበት፥ ወንዙም ወደማይደርቅበት ሸለቆ ይዘዋት ወርደው በዚያ አንገትዋን በመቈልመም ይስበሩት፤
ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት ጥጆችን አዘጋጁ፤ ጥጆቹን ጠምዳችሁ ሠረገላው የሚሳብበትን ጫፍ በቀንበሩ ላይ እሰሩት፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሱ፤