እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።
ዘዳግም 10:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በተራራው ግርጌ ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን በእሳት ውስጥ ሆኖ የገለጠላችሁን ዐሥሩን ትእዛዞች እንደ ቀድሞው ጽሑፍ አድርጎ በአሁኖቹ ጽላቶች ላይ ጻፈ፤ ጽላቶቹንም ለእኔ ሰጠኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በስብሰባው ቀን፣ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የተናገራቸውንና ቀድሞ ጽፏቸው የነበሩትን ዐሥሩን ትእዛዞች በእነዚህ ጽላት ላይ ጻፋቸው። እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥርቱን ቃላት ጌታ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገራችሁ ተሰብስባችሁበት በነበረበት ቀን፥ ቀድሞ ተጽፈው እንደነበረው በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፥ እነርሱንም ጌታ ለእኔ ሰጠኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በተራራው ላይ በእሳት መካከል የተናገራችሁን ዐሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቱ ላይ ጻፈ፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስብሰባ ተደርጎ በነበረበትም ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ የተናገራችሁን አሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ። |
እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ቅረጽ፤ እኔም አንተ በሰበርካቸው ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ።
ሙሴም ምንም ሳይበላና ሳይጠጣ ከእግዚአብሔር ጋር አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየ፤ ጌታም በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳን ቃላት የሆኑትን ዐሥሩን ትእዛዞች ጻፈ።
“በሲና ተራራ ላይ በተሰበሰባችሁበት ቀን እሞታለሁ ብለህ በመፍራት እግዚአብሔር ዳግመኛ እንዳይናገርህና የመገለጡን ሁኔታ የሚያመለክተውን አስፈሪ እሳት እንዳታይ ጠይቀህ ነበር።
ከዚያም በኋላ እናንተ በተራራው ግርጌ በተሰበሰባችሁ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሰማችሁትን ቃል በእጁ የጻፈባቸውን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ።