አሞጽ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብን ገዢና የአገሪቱንም ሹማምንት አጠፋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዥዋን እደመስሳለሁ፣ አለቆቿንም ሁሉ ከንጉሧ ጋራ እገድላለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈራጅንም ከመካከልዋ አጠፋለሁ፥ ከእርሱም ጋር አለቆችዋን ሁሉ እገድላለሁ፥” ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈራጅንም ከመካከልዋ አጠፋለሁ፤ ከእርሱም ጋር አለቆችዋን ሁሉ እገድላለሁ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈራጅንም ከመካከልዋ አጠፋለሁ፥ ከእርሱም ጋር አለቆችዋን ሁሉ እገድላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
“የሞአብ ሕዝብ ሆይ! በኀይላችሁና በሀብታችሁ ብዛት ተማምናችሁ ነበር፤ አሁን ግን እነሆ እናንተ ራሳችሁ እንኳ ትማረካላችሁ፤ ከሞሽ ተብሎ የሚጠራው ጣዖት ከልዑላን መሳፍንትና ከካህናቱ ጋር ተማርኮ ይወሰዳል።
በደላችሁ ምን ያኽል እንደ በዛና ኃጢአታችሁም ምን ያኽል ከባድ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ደጋግ ሰዎችን ታስጨንቃላችሁ፤ ጉቦ እየተቀበላችሁ በየፍርድ አደባባዩ የምስኪኖችን ፍትሕ ታጣምማላችሁ።
ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።
አየዋለሁ፤ ነገር ግን አሁን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፤ ግን በቅርብ አይደለም፤ ኮከብ ከያዕቆብ፥ በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይወጣል። የሞአብን ድንበር፥ የሴትንም ዘሮች ሁሉ ይደመስሳል።