ከዚህ በኋላ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ በመምታት “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
ሐዋርያት ሥራ 13:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በግሪክ ቋንቋ “ኤሊማስ” ተብሎ የሚጠራው ጠንቋይ ባርየሱስ አገረ ገዢው እንዳያምን ፈልጎ በርናባስንና ሳውልን ተቃወማቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠንቋዩ ኤልማስ ግን፣ የስሙ ትርጕም እንዲህ ነበርና፣ አገረ ገዥው እንዳያምን ለማደናቀፍ ስለ ፈለገ ተቃወማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠንቋዩ ግን ኤልማስ፥ ስሙ እንዲሁ ይተረጐማልና፥ አገረ ገዡን ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ ተቃወማቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስማተኛው ኤልማስም የስሙ ትርጓሜ እንዲህ ነበረና፥ ገዥውን ከማመን ሊከለክለው ፈልጎ ተቃወማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠንቋዩ ግን ኤልማስ፥ ስሙ እንዲሁ ይተረጐማልና፥ አገረ ገዡን ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ ተቃወማቸው። |
ከዚህ በኋላ የከናዕና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀረብ ብሎ በጥፊ በመምታት “ኧረ ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ?” አለው።
በዚሁ ዘመን፥ ማለትም ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር የገባዖን ሰው የሆነው የዐዙር ልጅ ሐናንያ በቤተ መቅደስ ተናገረኝ፤ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦
በዚያች ከተማ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው በከተማይቱ ውስጥ አስማት እያደረገ የሰማርያን ሕዝብ ሲያስደንቅ ቈይቶአል፤ “እኔ ትልቅ ሰው ነኝ!” እያለም ይናገር ነበር።
በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አንዲት አማኝ ነበረች፤ የስሟም ትርጒም በግሪክኛ ዶርቃ ትርጒሙም ሚዳቋ ማለት ነው፤ እርስዋ መልካም ነገር ማድረግና ለድኾች መለገሥ የምታዘወትር ሴት ነበረች፤
ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደ ተቃወሙት እነዚህ ሰዎች አእምሮአቸው የተበላሸና በእምነትም ነገር ውድቀት የደረሰባቸው ስለ ሆነ እውነትን ይቃወማሉ።