Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 13:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የሚኖረውም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባለው አስተዋይ አገረ ገዢ ጋር ነበረ፤ ይህ አገረ ገዢ በርናባስንና ሳውልን አስጠርቶ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈለገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እርሱም ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አስተዋይ አገረ ገዥ ጋራ ነበረ። ይህ አገረ ገዥ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈልጎ በርናባስንና ሳውልን አስጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እርሱም አስተዋይ ሰው ከሆነው ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባለው አገረ ገዥ ጋር ነበረ። ይህም በርናባስንና ሳውልን ወደ እርሱ ጠርቶ የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ፈለገ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እር​ሱም ብልህ ሰው በሆነ ሰር​ግ​ዮስ ጳው​ሎስ በሚ​ባል አገረ ገዢ ዘንድ ይኖር ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ሊሰማ ወድዶ በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን ወደ እርሱ ጠራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እርሱም አስተዋይ ሰው ከሆነው ሰርግዮስ ጳውሎስ ከሚባለው አገረ ገዥ ጋር ነበረ። ይህም በርናባስንና ሳውልን ወደ እርሱ ጠርቶ የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ፈለገ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 13:7
11 Referencias Cruzadas  

ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉት አንጥረኞች የሚከሱት ሰው ካለ ፍርድ የሚሰጥባቸው ቀኖች አሉ፤ ባለሥልጣኖችም አሉ፤ እዚያ ይሟገቱ።


አገረ ገዢውም የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ አመነ፤ ስለ ጌታ በሰማውም ትምህርት ተደነቀ።


ጋልዮስ የአካይያ ገዢ ሆኖ በተሾመ ጊዜ አይሁድ በአንድነት ተባብረው በጳውሎስ ላይ ተነሡ፤ ወደ ፍርድ ሸንጎ ወሰዱትና፥


የጥበበኛ ሰው ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፤ የአስተዋዮችም ጆሮ ጥበብን ይፈልጋል።


ነገር ግን በግሪክ ቋንቋ “ኤሊማስ” ተብሎ የሚጠራው ጠንቋይ ባርየሱስ አገረ ገዢው እንዳያምን ፈልጎ በርናባስንና ሳውልን ተቃወማቸው።


ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ።


ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።


አላዋቂዎች የስንፍናቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ ብልኆች ግን ዕውቀትን እንደ አክሊል ይቀዳጃሉ።


ሞኝ ሰው የሚነግሩትን ሁሉ አምኖ ይቀበላል፤ ብልኆች ግን እርምጃቸውን በጥንቃቄ ይመረምራሉ።


የብልኅ ሰው ጥበብ መንገዱን እንዳይስት ያደርገዋል። ሞኝን ሰው ግን ሞኝነቱ መንገዱን እንዲስት ያደርገዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios