ስለዚህም ዳዊት ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ለሚገኙት መኳንንቱ ሁሉ “ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ ከፈለግን በፍጥነት ከዚህ ሸሽተን እንውጣ! እንግዲህ ፍጠኑ! አለበለዚያ በፍጥነት መጥቶ ድል ይመታናል፤ በከተማይቱ ያገኘውንም ሁሉ ይገድላል!” አላቸው።
2 ሳሙኤል 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመላ አገሪቱም ሕዝቡ እርስ በርስ መጣላት ጀመረ፤ እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፦ “ንጉሥ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ አድኖናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አውጥቶናል፤ አሁን ግን ከአቤሴሎም ፊት በመሸሽ አገሪቱን ትቶ ሄዶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመላው የእስራኤል ነገዶችም፣ ሕዝቡ እንዲህ እያለ እርስ በርሱ ይከራከር ነበር፤ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ የታደገን እርሱ ነው፤ አሁን ግን በአቤሴሎም ምክንያት ከአገር ሸሽቶ ሄዷል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በበሩ አጠገብ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም፥ “እነሆ ንጉሡ በበሩ አጠገብ ተቀምጦአል” ተብሎ በተነገረ ጊዜ ሕዝቡ በሙሉ ወደ ንጉሡ መጣ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየቤታቸው ሸሽተው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመላው ነገደ እስራኤል የተሰበሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ ታድጎናል፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁንም ስለ አቤሴሎም ከሀገሩና ከመንግሥቱ ሸሸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ ሸሽቶ ነበር። ሕዝቡም ሁሉ በእስራኤል ነገድ ሁሉ ውስጥ፦ ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ ታድጎናል፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፥ አሁንም ስለ አቤሴሎም ከአገር ሸሽቶአል። |
ስለዚህም ዳዊት ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ለሚገኙት መኳንንቱ ሁሉ “ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ ከፈለግን በፍጥነት ከዚህ ሸሽተን እንውጣ! እንግዲህ ፍጠኑ! አለበለዚያ በፍጥነት መጥቶ ድል ይመታናል፤ በከተማይቱ ያገኘውንም ሁሉ ይገድላል!” አላቸው።
የአቤሴሎምንም ሬሳ ወስደው በደን ውስጥ በሚገኘው ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በእርሱም ላይ ብዙ ትልልቅ ድንጋይ ከምረው እንዲሸፈን አደረጉት፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ሸሽተው እያንዳንዱ ሰው ወደየቤቱ ገባ።
መሪያችን ይሆን ዘንድ አቤሴሎምን ቀብተን አንግሠነው ነበር፤ ነገር ግን እርሱ በጦርነት ላይ ተገደለ፤ ታዲያ፥ ንጉሥ ዳዊትን መልሶ ለማምጣት የሚሞክር ሰው እንዴት ታጣ?”
ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ወርዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል ካደረገ በኋላ “እግዚአብሔር በጠላቶቼ መካከል እንደ ጐርፍ ሰባብሮ ገባ” አለ፤ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “ባዓል ፈራጺም” ተብሎ ተጠራ።
እኔ ከወርቅ የተሠሩ ጌጣጌጦቻቸውን አውልቀው እንዲያመጡልኝ ነገርኳቸው፤ እነርሱም ያላቸውን ጌጣጌጥ ሁሉ አመጡልኝ፤ ጌጣጌጦቹንም ወደ እሳት ውስጥ በጣልኳቸው ጊዜ ይህ የጥጃ ምስል ወጣ።”
ሳኦልም እንደ ገና “ንጉሡ ስለ ልጁ ከአንተ የሚፈልገው ጥሎሽ ጠላቶቹን መበቀል እንዲችል አንድ መቶ ፍልስጥኤማውያን ገድለህ ሸለፈታቸውን እንድታመጣለት ብቻ ነው” ብላችሁ ንገሩት ሲል ባለሟሎቹን አዘዘ። ሳኦል ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲገደልለት በማቀድ ነበር።
እርሱ ለሕይወቱ ሳይሳሳ በመጋፈጥ ጎልያድን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ታላቅ ድልን አቀዳጀ፤ አንተም ይህን ባየህ ጊዜ ደስ ብሎህ ነበር፤ ታዲያ አሁን አንተ በንጹሕ ሰው ላይ በደል ለመሥራት ስለምን ታስባለህ? ምክንያት በሌለውስ ነገር ዳዊትን ለመግደል ስለምን ፈለግኽ?”