2 ቆሮንቶስ 9:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የዐካይያ ሰዎች ከዐለፈው ዓመት ጀምረው ለመርዳት ዝግጁዎች ናቸው” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ ስለ እናንተ የምመካው ትጋታችሁን ስለማውቅ ነው፤ የእናንተም ትጋት ሌሎችን አነሣሥቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ሌሎችን ለመርዳት ያላችሁን በጎ ፈቃድ ዐውቃለሁ፤ ካለፈው ዓመት ጀምሮ እናንተ በአካይያ የምትኖሩ ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ እንደ ሆናችሁ ለመቄዶንያ ሰዎች አፌን ሞልቼ ተናግሬአለሁ፤ ቅን ፍላጎታችሁም ብዙዎችን ለበጎ ሥራ አነሣሥቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎ ፈቃዳችሁን ስለማውቅ፤ በእናንተ ላይ የምመካበትን ምክንያት ለመቄዶንያ ሰዎች፥ “አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቶአል፤” ብዬ ተናግሬለሁ፤ ቅንዐታችሁም ብዙዎችን አነሣሥቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ እንደምትተጉ አውቃለሁና፤ ስለዚህም “የአካይያ ሰዎች እኮ ከአምና ጀምሮ አዘጋጅተዋል” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ አመሰገንኋችሁ፤ እነሆም የእናንተ መፎካከር ብዙዎችን ሰዎች አትግቶአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጎ ፈቃዳችሁን አውቄአለሁና፤ ስለዚህም፦ አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቶአል ብዬ ለመቄዶንያ ሰዎች በእናንተ እመካለሁ፥ ቅንዓታችሁም የሚበዙቱን አነሣሥቶአል። |
ወንድሞች ሆይ! የእስጢፋኖስ ቤተሰብ በአካይያ አገር የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ምእመናንን ለማገልገል ራሳቸውን አሳልፈው እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፥ በቆሮንቶስ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንና እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ፥
በእናንተ የነበረኝን ትምክሕት ለቲቶ ነግሬው ነበር፤ እናንተም አላሳፈራችሁኝም፤ ሁልጊዜ እውነትን እንነግራችሁ ነበር፤ ይህም ስለ እናንተ ለቲቶ የነገርነው ትምክሕት እውነት በመሆኑ ተረጋግጦአል።
በእናንተ ላይ ያለኝ እምነት ከፍተኛ ነው፤ በእናንተ ላይ ያለኝ ትምክሕት ትልቅ ነው፤ በእናንተም እጽናናለሁ፤ በመከራችን ሁሉ በጣም እደሰታለሁ።
በዚህ ጉዳይ ለእናንተ መልካም መስሎ የታየኝን ምክር እሰጣችኋለሁ፤ ባለፈው ዓመት ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ይህን ለማድረግ በመጀመሪያ የፈለጋችሁት እናንተ ነበራችሁ።
ከዚህም በላይ ይህ ወንድም እኛ ይህን በጎ ሥራ ለጌታ ክብር ስንፈጽምና ለማገልገል ያለንንም መልካም ፈቃድ ስንገልጥ አብሮን በመሄድ የሥራ ተካፋያችን እንዲሆን በአብያተ ክርስቲያን የተመረጠ ነው።
ስለዚህ ፍቅራችሁን ግለጡላቸው፤ በዚህ ዐይነት ፍቅራችንና በእናንተ ላይ ያለን ትምክሕት ከንቱ አለመሆኑን ለአብያተ ክርስቲያን ሁሉ ታሳያላችሁ።
ታዲያ፥ ይህን የምላችሁ በማዘዝ አይደለም፤ ነገር ግን የሌሎችን የመስጠት ትጋት ከእናንተ ትጋት ጋር በማወዳደር የእናንተን ፍቅር እውነተኛነት ለማረጋገጥ ብዬ ነው።