የእኔ ከተማ ግን ታላቅ ከተማ ናት፤ በእስራኤል ሰላም የሰፈነባትና ታማኝ ከተማ እርስዋ ናት፤ ታዲያ፥ አንተ ይህችን ከተማ ለመደምሰስ ለምን ታቅዳለህ? የእግዚአብሔር ርስት የሆነውን ነገር ለማፍረስ ትፈልጋለህን?”
1 ጢሞቴዎስ 2:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን በመፍራትና በመልካም ጠባይ እየተመራን በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር በተለይ ለነገሥታትና በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይኸውም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም እግዚአብሔርን በመምሰልና በተገባ አካሄድ ሁሉ፥ ጸጥታ የሰፈነበትና ሰላማዊ የሆነ ሕይወት እንዲኖረን ስለ ነገሥታትና በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ስላሉ ሁሉ ጸሎት እናቅርብ። |
የእኔ ከተማ ግን ታላቅ ከተማ ናት፤ በእስራኤል ሰላም የሰፈነባትና ታማኝ ከተማ እርስዋ ናት፤ ታዲያ፥ አንተ ይህችን ከተማ ለመደምሰስ ለምን ታቅዳለህ? የእግዚአብሔር ርስት የሆነውን ነገር ለማፍረስ ትፈልጋለህን?”
እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
ተማርካችሁ ሄዳችሁ እንድትኖሩባቸው ላደረግኋቸው ከተሞችም ዕድገት መልካም ነገርን ተመኙ፤ ስለ እነርሱም መልካም ኑሮ ወደ እኔ ጸልዩ፤ እነርሱ መልካም ኑሮ ቢኖሩ እናንተም መልካም ኑሮን ትኖራላችሁ።
በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ሕይወቱን ለእግዚአብሔር የሰጠ ጻድቅ ሰው ነበር፤ የእስራኤልን የመዳን ተስፋ ይጠባበቅ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር።
እነርሱም “እኛ የመጣነው ከመቶ አለቃው ከቆርኔሌዎስ ዘንድ ነው፤ እርሱ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ የሚያከብረው እግዚአብሔርን የሚያመልክ ደግ ሰው ነው፤ አንተን ወደ ቤቱ አስጠርቶ የምትለውን እንዲሰማ ቅዱስ መልአክ ገልጦ ነግሮታል” አሉት።
አእምሮአችሁ በእነዚህ ከሁሉ በሚበልጡና በሚያስመሰግኑ መልካም ነገሮች የተመላ ይሁን፤ በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ፥ ክቡር፥ ትክክለኛ፥ ንጹሕ፥ አስደሳችና ምስጉን የሆኑ ነገሮችን ሁሉ አስቡ።