1 ሳሙኤል 7:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል ተከለው፦ እግዚአብሔር እስካሁን ረድቶናል ለማለት ስሙን አቤንዔዜር ብሎ ሰየመው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ ስሙንም “እግዚአብሔር እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው፤ “ጌታ እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል” ሲል ስሙን “አቤንኤዘር” ብሎ ጠራው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በመሴፋና በአሮጌው ከተማ መካከል አኖረው፤ ስሙንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል” ሲል “አቤንኤዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድኤት ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፥ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው። |
በዚያን ጊዜ በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ እንዲሁም በግብጽ ጠረፍ ላይ ለእግዚአብሔር የተለየ የድንጋይ ዐምድ ይተከላል።
እስከ ዛሬ ድረስ የእግዚአብሔር ርዳታ አልተለየኝም፤ ስለዚህ ለትንሹም ለትልቁም እየመሰከርኩ እዚህ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ አስቀድመው እንዲህ ይሆናል ያሉትን ከመናገር በቀር ሌላ ምንም አልተናገርኩም።
ኢያሱም ደግሞ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በቆሙበት በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዐሥራ ሁለት የመታሰቢያ ድንጋዮችን አቆሙ፤ እነዚያም ድንጋዮች እስከ ዛሬ በዚያው ይገኛሉ፤
እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወጡ፤ ስለዚህም እስራኤላውያን አቤንዔዜር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም አፌቅ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሰፈሩ፤