1 ሳሙኤል 22:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም፥ “የአሒጡብ ልጅ ሆይ! እንግዲህ ስማ” አለው። አቤሜሌክም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” ብሎ መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፤ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ፤ እንግዲህ ስማ” አለው። አቢሜሌክም፣ “ዕሺ ጌታዬ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፤ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ፤ እንግዲህ ስማ” አለው። አቢሜሌክም፥ “እሺ ጌታዬ” ብሎ መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “የአኪጦብ ልጅ ሆይ! እንግዲህ ስማ” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ ጌታዬ ሆይ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ የአኪጦብ ልጅ ሆይ፥ እንግዲህ ስማ አለ፥ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ጌታዬ ሆይ ብሎ መለሰ። |
የሳኦል የልጅ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ መፊቦሼት በመጣ ጊዜ በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት አክብሮቱን ገለጠ። ዳዊትም “መፊቦሼት!” ሲል ጠራው። መፊቦሼትም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ላልጠየቁኝ ተገለጥኩላቸው፤ ላልፈለጉኝም ተገኘሁላቸው፤ ስሜንም ላልጠራ ሕዝብ ‘እነሆ፥ እዚህ አለሁ፥ እነሆ፥ እዚህ አለሁ’ አልኳቸው።
ስለዚህም ንጉሥ ሳኦል ወደ ካህኑ የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክና በኖብ ወደሚገኙት ዘመዶቹ ወደሆኑት ካህናት ሁሉ መልእክት ላከ፤ እነርሱም መጡ፤
ሳኦልም “አንተና የእሴይ ልጅ በእኔ ላይ ያሤራችሁት ስለምንድን ነው? ለእርሱ ምግብና ሰይፍ ሰጥተኸዋል እግዚአብሔርንም ጠይቀህለታል፤ እነሆ፥ እርሱ አሁን በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶ እኔን ለመግደል አጋጣሚ ጊዜ በመፈለግ ላይ ነው” ሲል ጠየቀው።
ሳኦልም ባለሟሎችን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የብንያም ሰዎች አድምጡኝ! በውኑ የእሴይ ልጅ ዳዊት ለሁላችሁም ለእያንዳንዳችሁ የእርሻ መሬትና የወይን ተክል ቦታ የሚሰጣችሁና በሠራዊቱም ውስጥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች አድርጎ የሚሾማችሁ ይመስላችኋልን?