La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 17:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጦሩ ዘንግ ውፍረቱ የሸማኔ መጠቅለያ ያኽል ነበር፤ የጦሩም ብረት ክብደቱ ሰባት ኪሎ ያኽል ነበር፤ ጋሻውንም ጋሻጃግሬው ተሸክሞለት በፊት በፊቱ ይሄድ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጦሩም ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የወፈረ፣ የጦሩም ብረት ስድስት መቶ ሰቅል ያህል የሚመዝን ነበር፤ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጦሩም ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የወፈረ፥ የጦሩም ብረት ስድስት መቶ ሰቅል ያህል የሚመዝን ነበር፤ ጋሻ ጃግሬውም ከፊት ከፊቱ ይሄድ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የጦ​ሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠ​ቅ​ለያ ነበረ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ስድ​ስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጦሩም የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅልያ ነበረ፥ የጦሩም ሚዛን ስድስት መቶ ሰቅል ብረት ነበረ፥ ጋሻ ጃግሬውም በፊቱ ይሄድ ነበር።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 17:7
5 Referencias Cruzadas  

ሦስት ኪሎ ተኩል የሚመዝን ከነሐስ የተሠራ ጦር የያዘና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ዩሽቢበኖብ ተብሎ የሚጠራ አንድ ኀያል ሰው ዳዊትን ለመግደል አስቦ ነበር፤


ቀጥሎም በጎብ ሌላ ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተደረገ፤ በዚህም ጊዜ የቤተልሔም ተወላጅ የሆነው የያዒር ልጅ ኤልሐናን የጋት ተወላጅ የሆነውንና የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን ጎልያድ ተብሎ የሚጠራውን ሌላ ፍልስጥኤማዊ ገደለ።


እንዲሁም በጣም ትልቅ ጦር ይዞ የነበረውን፥ ቁመቱ ከሁለት ሜትር በላይ የሆነውን፥ አንድ ግዙፍ ግብጻዊ ገድሎአል፤ ይኸውም በናያ በእጁ ከበትር በስተቀር ሌላ የጦር መሣሪያ ሳይዝ ወደ ግብጻዊው ቀርቦ ከመታው በኋላ ግብጻዊው ይዞት የነበረውን የሸማኔ መጠቅለያ የሚመስለውን የገዛ ጦሩን ቀምቶ ገደለው።


በፍልስጥኤማውያን ላይ የተደረገ ሌላም ጦርነት ነበረ፤ በዚያን ጊዜ የያዒር ልጅ ኤልሐናን የጋት ተወላጅ የሆነውን የጦሩ እጀታ ውፍረቱ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።


ፍልስጥኤማዊው ጎልያድ ወደ ዳዊት ለመቅረብ መራመድ ጀመረ፤ ጋሻጃግሬውም በፊት በፊቱ ይሄድ ነበር፤