1 ሳሙኤል 17:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነሐስ የተሠራና ክብደቱ ኀምሳ ሰባት ኪሎ የሚሆን ጥሩርና ከነሐስ የተሠራ የራስ ቊር ነበረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ከናስ የተሠራ የራስ ቍር ደፍቶ፣ ክብደቱ ዐምስት ሺሕ ሰቅል የሆነ የናስ ጥሩር ለብሶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ከናስ የተሠራ የናስ ቁር ደፍቶ፥ ክብደቱ አምስት ሺህ ሰቅል የሆነ የናሐስ ጥሩርም ለብሶ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በራሱም የናስ ቍር ደፍቶ ነበር፤ ጥሩርም ለብሶ ነበር፤ የጥሩሩም ሚዛን አምስት ሺህ ሰቅል ናስና ብረት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራሱም የናስ ቁር ደፍቶ ነበር፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር፥ የጥሩሩም ሚዛን አምስት ሺህ ሰቅል ናስ ነበረ። |
ከጋት ከተማ የመጣ፥ ጎልያድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ግዙፍ ሰው፥ ከፍልስጥኤማውያን ሰፈር ወጥቶ እስራኤላውያንን መፈታተን ጀመረ፤ የዚያም ሰው ቁመት ሦስት ሜትር ያኽል ነበር፤