1 ነገሥት 1:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናታንም፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዶንያስ ከአንተ በኋላ ነግሦ በዙፋንህ እንዲቀመጥ አስታውቀሃልን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ናታንም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ ለመሆኑ አዶንያስ ከአንተ ቀጥሎ እንደሚነግሥ፣ በዙፋንህም እንደሚቀመጥ አስታውቀሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናታንም አለ፦ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ፦ ከእኔ በኋላ አዶንያስ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ላይ ይቀመጣል ብለሃልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢዩ ናታንም አለ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፦ አንተ ከእኔ በኋላ አዶንያስ ይነግሣል፥ በዙፋኔ ላይም ይቀመጣል ብለሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናታንም አለ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አንተ ‘ከእኔ በኋላ አዶንያስ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ላይ ይቀመጣል፤’ ብለሃልን? |
አዶንያስ በዛሬው ዕለት ብዙ ጥጆችንና የሰቡ ኰርማዎችን፥ በጎችን ዐርዶ መሥዋዕት አቅርቦአል፤ ሌሎቹን የንጉሡን ልጆች የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዞአል፤ እነሆ አሁን በዚህ ሰዓት “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ አዶንያስ!” በማለት እየደነፉ ከእርሱ ጋር በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው።
ከአቤሴሎም በኋላ ከዳዊትና ከሐጊት የተወለደ በሕይወት ያለ ተከታይ ልጅ አዶንያስ ነበር፤ እርሱም እጅግ መልከ ቀና ነበር፤ ዳዊት ስለማናቸውም ነገር ምክርና ተግሣጽ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አዶንያስ ለመንገሥ ፈለገ፤ ይህንንም ፍላጎቱን ለማሟላት ሠረገሎችን፥ ፈረሶችንና ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎችን አዘጋጀ።