ሣራይም አብራምን “የደረሰብኝ በደል በአንተ ላይ ይሁን፤ እርስዋን ለአንተ የሰጠሁህ እኔ ራሴ ነኝ፤ እርስዋ ግን መፅነስዋን ካወቀችበት ጊዜ አንሥቶ እኔን መናቅ ጀምራለች፤ አሁንም ከእኔና ከአንተ ጥፋተኛው ማን እንደ ሆነ እግዚአብሔር ይፍረድ!” አለችው።
1 ነገሥት 1:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ባለሟሎቹ “ንጉሥ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣልህ፤ ከአንተ ጋር ዐቅፋህ በመተኛት ታሞቅሃለች” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አገልጋዮቹ፣ “ንጉሡን የምትንከባከብና የምታገለግል ወጣት ድንግል እንፈልግ፤ እርሷም ጌታችን ንጉሡ እንዲሞቀው በጐኑ ትተኛለች” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎቹም፦ “ንጉስ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣ፤ በጌታችንም በንጉሡ እቅፍ ተኝታ ታሞቅሃለች” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊት አሽከሮችም፥ “ለጌታችን ለንጉሡ ድንግል ልጅ ትፈለግለት፤ በንጉሡም ፊት ቆማ ታገልግለው፥ በጌታችንም በንጉሡ ብብት ተኝታ ትቀፈው፤ ታሙቀውም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቹም “ለጌታችን ለንጉሡ ድንግል ትፈለግለት፤ በንጉሡም ፊት ቆማ ታገልግለው፤ በጌታችንም በንጉሡ ብብት ተኝታ ታሙቀው፤” አሉት። |
ሣራይም አብራምን “የደረሰብኝ በደል በአንተ ላይ ይሁን፤ እርስዋን ለአንተ የሰጠሁህ እኔ ራሴ ነኝ፤ እርስዋ ግን መፅነስዋን ካወቀችበት ጊዜ አንሥቶ እኔን መናቅ ጀምራለች፤ አሁንም ከእኔና ከአንተ ጥፋተኛው ማን እንደ ሆነ እግዚአብሔር ይፍረድ!” አለችው።
ድኻው ግን በገንዘቡ የገዛት አንዲት የበግ ግልገል ብቻ ነበረችው፤ እርስዋን እየተንከባከበ ከልጆቹ ጋር በቤቱ ውስጥ ያሳድጋት ነበር፤ ከሚመገበው ይመግባት፥ ከሚጠጣውም ያጠጣት ነበር፤ ስትተኛም ያቅፋት ነበር፤ ያቺም ግልገል ልክ እንደ ልጁ ነበረች፤
አንዲት ቈንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፍለጋ ተደረገ፤ ሹኔም ተብላ ከምትጠራው ስፍራ አቢሻግ የምትባል አንዲት ልጃገረድ አግኝተው ለንጉሡ አመጡለት፤
ልጆቼ ሆይ! በፊቱ ቆማችሁ እንድታገለግሉትና የእርሱ አገልጋዮች እንድትሆኑ፥ መሥዋዕትንም እንድታቀርቡ እግዚአብሔር የመረጣችሁ ስለ ሆነ እንግዲህ ቸልተኞች አትሁኑ።”
በሰው ላይ እምነትህን አትጣል፤ በቅርብ ወዳጅህም አትተማመን፤ አቅፈሃት ለምትተኛው ሚስትህ የምትናገረው ቃል እንኳ ጥንቃቄ የተሞላበት ይሁን።
በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።
“በቅርብም ሆነ በሩቅ ካሉት፥ ከአንዱ የምድር ዳርቻ በአካባቢህ ካሉ ከአሕዛብ አማልክት አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን አንዱን እናምልክ በማለት ሌላ እንኳ ቀርቶ የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ በምሥጢር ይገፋፋህ ይሆናል።