አንተ የጥበብህ ፍሬዎች እንዲባክኑ አትሻም፤ ከዚህም የተነሣ ሰዎች በትንሿ የእንጨት ስባሪ ተማምነው ማዕበሉን በታንኳ ያቋርጣሉ፤ እንዲያም ሆኖ ግን ካሰቡበት በደኀና ይደርሳሉ።
የጥበብህ ሥራው ስንፍና እንዳይሆን ትወዳለህ፥ ስለዚህ ሰዎች ሰውነታቸውን በተናቀና በተዋረደ እንጨት ተማምነው በታላቅና በታናሽ መርከብ በሞገዱ መካከል ተሻግረው ይድናሉ።