ተስፋቸውን በሙት ነገሮች ላይ የሚያደርጉ፥ ወርቅም ይሁን ብር፥ የእንስሳት ምስሎችን፥ ጥንት በሰው እጅ የተቀረጹ ዋጋ የሌላቸው ድንጊያዎችን የሚያመልኩ ሁሉ ምስኪኖች ናቸው።
ከወርቅና ከብር በጥበብ የተሠሩ የሰው እጅ ሥራዎችን፥ የእንስሳ ምሳሌን፥ ወይም የማይጠቅም የጥንት የእጅ ሥራ ድንጋይን አማልክት ብለው የሚጠሩ እነዚህ ጐስቋሎች ናቸው፥ ተስፋቸውም በሞቱ ነገሮች ላይ ነው።