ለዐይን ደስ የሚያሰኝ የቅድስና ማኀተም የተቀረጸበት፥ እጅግ ያጌጠና የድንቅ ሥራ ውጤት የሆነ፥ በጥምጥሙ ላይ የሚያርፍ የወርቅ አክሊልም ሰጠው።
በማኅተም መልክ አምሳል የተሠራ የወርቅ አክሊልን በዝግራ መጠምጠሚያው ላይ አደረገለት፤ የተለየ የክብሩ መመኪያ የሚሆን ተአምራት የሚያደርግበት፥ ለዐይን የተወደደ፥ ጌጡ ፈጽሞ ያማረ የወርቅ መጠምጠሚያን በዝግራ መጠምጠሚያው ላይ አደረገለት።