ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ መልካቸውን ትንቃለህ።
ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ ጌታ ሆይ፤ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣ እንደ ቅዠት ከንቱ ታደርጋቸዋለህ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ስትነሣ እነርሱ በማለዳ እንደሚረሳ ሕልም ይጠፋሉ።
ወደ ኪዳንህም ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኃጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና።
እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፥ እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል።
እነሆ፥ ዘመኖቼን ከእጅ መዳፍ አሳጠርካቸው፥ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ነው።
ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።
ጌታ ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ በወይን ኃይል እንደተበረታታ ጀግና፥
ታጥለቀልቃቸዋለህ፥ እንደ ሕልም ናቸው፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ሣር።