La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 36:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ስለ ሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ ‘የወደዱትን ያግቡ፤ ነገር ግን ከአባታቸው ወገን ከሆነ ነገድ ብቻ ያግቡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንግዲህ የሰለጰዓድን ሴት ልጆች በተመለከተ እግዚአብሔር የሚያዝዘው ይህ ነው፤ ከአባታቸው ነገድ ወገን እስከ ሆነ ድረስ የወደዱትን ማግባት ይችላሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ እግዚአብሔር ‘የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ከገዛ ነገዳቸው ወገን እስከ ሆነ ድረስ የወደዱትን ማግባት ይችላሉ’ ይላል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፤ የወ​ደ​ዱ​ትን ያግቡ፤ ነገር ግን ከአ​ባ​ታ​ቸው ነገድ ብቻ ያግቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር ስለ ሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ያዘዘው ነገር ይህ ነው፤ የወደዱትን ያግቡ፤ ነገር ግን ከአባታቸው ነገድ ብቻ ያግቡ።

Ver Capítulo



ዘኍል 36:6
7 Referencias Cruzadas  

“እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፥


አልዓዛርም ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ፤ ወንድሞቻቸውም የቂስ ልጆች አገቡአቸው።


“የሰለጰዓድ ልጆች ትክክለኛ ነገር ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ወደ እነርሱ ይተላለፍ።


ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ልጆች ወገኖች ባሎቻቸውን አገቡ፥ ርስታቸውም በአባታቸው ነገድ ጸና።


ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንደ ጌታ ቃል እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “የዮሴፍ ልጆች ነገድ እውነት የሆነን ነገር ተናግረዋል።


ከማያምኑ ጋር አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋር ምን ድርሻ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?