La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 27:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አባቱም ወንድሞች ባይኖሩት ከወገኑ ለቀረበ ዘመድ ርስቱን ትሰጣላችሁ እርሱም ይውረሰው፤ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘ ለእስራኤል ልጆች ሥርዓትና ፍርድ ይሁን።’ ”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አባቱ፣ ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ከጐሣው መካከል ቅርብ ለሆነ ዘመዱ ይስጥ፤ እርሱም ይውረሰው። ይህም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ሕጋዊ መመሪያ ይሆናቸዋል።’ ”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወንድሞችም ሆኑ አጐቶች ከሌሉት የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው ንብረቱን ወርሶ ሊጠቀምበት ይችላል፤ እኔ እግዚአብሔር ባዘዝኩህ መሠረት የእስራኤል ሕዝብ ይህን ሕግና ሥርዓት ቋሚ መመሪያ አድርገው ይጠብቁት።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ባ​ቱም ወን​ድ​ሞች ባይ​ኖ​ሩት ከወ​ገኑ ለቀ​ረበ ዘመድ ርስ​ቱን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ እር​ሱም ይው​ረ​ሰው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ይሁን።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአባቱም ወንድሞች ባይኖሩት ከወገኑ ለቀረበ ዘመድ ርስቱን ስጡ እርሱም ይውረሰው፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ለእስራኤል ልጆች ሥርዓትና ፍርድ ይሁን።

Ver Capítulo



ዘኍል 27:11
7 Referencias Cruzadas  

እንደ ጌታም ቃል የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ፦ ‘በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፥ እባክህ፥ ግዛ፤ የርስቱና የመቤዠቱ መብት የአንተ ነውና፤ ለአንተ ግዛው’ አለኝ። ይህም የጌታ ቃል እንደሆነ አወቅሁ።


“ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል።


ወይም አጎቱ ወይም የአጎቱ ልጅ ይቤዠው፤ ወይም ከወገኑ የሥጋ ዘመዱ የሆነ ሰው ይቤዠው፤ ወይም እርሱ ቢበለጥግ ራሱን ይቤዥ።


ወንድሞችም ባይኖሩት ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ትሰጣላችሁ፤


“እነዚህም ነገሮች ለልጅ ልጃችሁ በማደሪያችሁ ሁሉ ሥርዓትና ፍርድ ይሁኑላችሁ።


ዳዊትም ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህን ለእስራኤል እንደ ሕግና ሥርዓት አደረገው።