በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙ፥ ለዘለዓለሙም እንዲያገለግሉት ጌታ ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የጌታን ታቦት ሊሸከም አይገባውም።”
ዘኍል 10:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀዓታውያንም የተቀደሱትን ዕቃዎች ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱም ከመምጣታቸው በፊት ማደሪያው ተተክሎ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ቀዓታውያን ንዋያተ ቅድሳቱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ከመድረሳቸው በፊት ማደሪያው ተተክሎ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሌዋዊው የቀዓት ጐሣ የሆኑት ሰዎች ንዋያተ ቅድሳትን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ወደሚቀጥለው ሰፈር ከመድረሳቸው በፊት ድንኳኑ እንደገና መተከል ነበረበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀዓትም ልጆች ንዋየ ቅድሳቱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነዚህም እስኪመጡ ድረስ እነዚያ ድንኳኑን ተከሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀዓታውያንም መቅደሱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነዚህም እስኪመጡ ድረስ እነዚያ ማደሪያውን ተከሉ። |
በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙ፥ ለዘለዓለሙም እንዲያገለግሉት ጌታ ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የጌታን ታቦት ሊሸከም አይገባውም።”
የጌታን ቤት አገልግሎት በሠሩ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመትና ከዚያም ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቆጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።
“ከዚያም በኋላ በሰፈሮቹም መካከል የመገናኛው ድንኳን ከሌዋውያን ሰፈር ጋር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው እያንዳንዱ ሰው ስፍራቸውን ይዘው በየዓላሞቻቸው ይጓዛሉ።