Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 10:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ቀዓታውያንም መቅደሱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነዚህም እስኪመጡ ድረስ እነዚያ ማደሪያውን ተከሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚህ በኋላ ቀዓታውያን ንዋያተ ቅድሳቱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ከመድረሳቸው በፊት ማደሪያው ተተክሎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ቀዓታውያንም የተቀደሱትን ዕቃዎች ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱም ከመምጣታቸው በፊት ማደሪያው ተተክሎ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ከዚህ በኋላ የሌዋዊው የቀዓት ጐሣ የሆኑት ሰዎች ንዋያተ ቅድሳትን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ወደሚቀጥለው ሰፈር ከመድረሳቸው በፊት ድንኳኑ እንደገና መተከል ነበረበት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የቀ​ዓ​ትም ልጆች ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን ተሸ​ክ​መው ተጓዙ፤ እነ​ዚ​ህም እስ​ኪ​መጡ ድረስ እነ​ዚያ ድን​ኳ​ኑን ተከሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 10:21
11 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜም ዳዊት “የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከሙ ዘንድ፥ ለዘላለሙም ያገለግሉት ዘንድ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከም ዘንድ አይገባውም፤” አለ።


የእግዚአብሔርን ቤት አገልግሎት በሠሩ ከሃያ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቈጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።


ማደሪያውም ሲነሣ ሌዋውያን ይንቀሉት፤ ማደሪያውም በሰፈረ ጊዜ ሌዋውያን ይትከሉት፤ ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።


ማደሪያውም ተነቀለ፤ ማደሪያውንም የተሸከሙ የጌድሶን ልጆችና የሜራሪ ልጆች ተጓዙ።


በጋድም ልጆች ነገድ ሠራዊት ላይ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ አለቃ ነበረ።


ከዚያም በኋላ የመገናኛው ድንኳን በሰፈሮቹም መካከል የሌዋውያን ሰፈር ይጓዛል፤ እንደ ሰፈራቸው ሰው ሁሉ በየስፍራው በየዓላማውም ይጓዛሉ።


ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋየ ቅድሳቱን ለድንገት እንኳ ለማየት አይግቡ።


ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos