ነህምያ 7:62 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የድላያ ልጆች፥ የጦቢያ ልጆች፥ የንቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳላያ፣ የጦብያና፣ የኔቆዳ ዘሮች 642 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች ስድስት መቶ አርባ ሁለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። |
ከቴልሜላሕ፥ ከቴል ሀርሻ፥ ከክሩብ፥ ከአዶንና ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤትና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፤
ከካህናቱም የሐባያ ልጆች፥ የሃቆጽ ልጆች፥ የባርዚላይ ልጆች እሱም ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ሴቶች ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ ነው።