ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንኩ አትዩኝ፥ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥ ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
ማርቆስ 4:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፤ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፤ ሥር ባለመስደዱም ደረቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ፀሐይ በወጣ ጊዜ ጠወለገ፤ የጠለቀ ሥር ስላልነበረውም ደረቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፤ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። |
ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንኩ አትዩኝ፥ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥ ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
የጨካኞችም ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፥ ለድሀው መጠጊያ፥ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መሸሸጊያ፥ ከውሽንፍር መጠለያ፥ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።
ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።
እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ነውር ናቸው፥ ራሳቸውን እየመገቡ ያለ ኀፍረት ከእናንተ ጋር ይጋበዛሉ፥ በነፋስ የሚገፉ ውሃ የሌላቸው ደመናዎች፥ በበጋ ፍሬ የማያፈሩ፥ ሁለት ጊዜ የሞቱ፥ ከሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ናቸው፤