Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፤ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ፀሓይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፤ ሥር ባለመስደዱም ደረቀ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፤ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይሁን እንጂ ፀሐይ በወጣ ጊዜ ጠወለገ፤ የጠለቀ ሥር ስላልነበረውም ደረቀ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 4:6
15 Referencias Cruzadas  

ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።


ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይጠሙም፤ ፀሐይም ትኵሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም፤


እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥


በእ​ርሱ ተመ​ሥ​ር​ታ​ችሁ ታነጹ፤ በም​ስ​ጋ​ናው ትበዙ ዘንድ፥ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሃይ​ማ​ኖት ጽኑ።


በል​ባ​ችሁ ውስጥ በፍ​ቅር ሥር መሠ​ረ​ታ​ችሁ የጸና ሲሆን ክር​ስ​ቶስ በሃ​ይ​ማ​ኖት በሰው ውስጥ ያድ​ራ​ልና።


ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ።


ለተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ከተ​ሞች ረዳት ሆነ​ሃ​ልና፥ በች​ግ​ራ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁ​ትን በደ​ስታ ጋረ​ድ​ሃ​ቸው፤ ከክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም አዳ​ን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ጠ​ሙት ጥላ ሆን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ገ​ፉ​ትም ሕይ​ወት ሆን​ሃ​ቸው።


ፀሓይ መል​ኬን አክ​ስ​ሎ​ታ​ልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አት​ዩኝ፤ የእ​ናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ች​ንም ጠባቂ አደ​ረ​ጉኝ፤ ነገር ግን የእ​ኔን የወ​ይን ቦታ አል​ጠ​በ​ቅ​ሁም።


ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።


ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤


ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፤ እሾህም ወጣና አነቀው፤ ፍሬም አልሰጠም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios