ሉቃስ 16:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ፥ አልዓዛርንም በእቅፉ አየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሲኦልም እየተሠቃየ ሳለ ቀና ብሎ ከሩቅ አብርሃምን አየ፤ አልዓዛርንም በዕቅፉ ይዞት አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሲኦልም ሲሠቃይ ሳለ፥ ቀና ብሎ አብርሃምንና አጠገቡም የነበረውን አልዓዛርን በሩቅ አያቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሲኦልም በሥቃይ ሳለ ዐይኖቹን አንሥቶ አብርሃምን ከሩቅ አየው፤ አልዓዛርንም በአጠገቡ ተቀምጦ አየው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ። |
እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው፥ እረኛቸውም ሞት ነው፥ ቅኖችም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች።
ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፥ የምድርንም ታላላቆች ሁሉ፥ ለአንተ አንቀሳቀሰች፥ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች።
አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን ኖሮ እስከ ዛሬ በቆየች ነበር።
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
እርሱም እየጮኸ ‘አብርሃም አባት ሆይ! ማረኝ፤ በዚህ ነበልባል እሠቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ላክልኝ፤’ አለ።
ኢየሱስንም ባየ ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅ ድምፅም፦ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ? እንዳታሰቃየኝ እለምንሃለሁ፤” አለ።
ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።