ዘሌዋውያን 4:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጁንም የኃጢአት መሥዋዕት በሆነችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአትን መሥዋዕት ያርዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጁን ለኀጢአት መሥዋዕት በቀረበችው ፍየል ራስ ላይ ይጫን፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራም ይረዳት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጁንም በእንስሳይቱ ራስ ላይ ይጫን፤ ከመሠዊያው በስተ ሰሜን ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ስፍራ ይረዳት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጁንም በኀጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ ለሚቃጠልም መሥዋዕት እንስሳትን በሚያርዱበት ስፍራ የኀጢአት መሥዋዕት ፍየልዋን ያርዳታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጁንም በኃጢአት መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአትን መሥዋዕት ያርዳል። |
በሬውንም በጌታ ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።