በሕዝቡ ላይ የሚሆነው እንዲሁ ካህኑ ላይ ይሆናል፤ በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው እንዲሁ በአስተዳዳሪው፥ በአገልጋይቱም የሚሆነው እንዲሁ በእመቤትዋ፥ በሸማቹ ላይ የሚሆነው እንዲሁ በሻጩ፥ በአበዳሪው የሚሆነው እንዲሁ በተበዳሪው፥ በዕዳ አስከፋዩም የሚሆነው እንዲሁ በዕዳ ከፋዩ ይሆናል።
ዘሌዋውያን 25:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርህን በወለድ አታበድረው፤ ምግብህንም በትርፍ አትሽጥለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገንዘብህን በዐራጣ አታበድረው፤ ምግብህንም በትርፍ አትሽጥለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምታበድረውም ገንዘብ ወለድ አትጠይቀው፤ በምትሸጥለትም ምግብ ትርፍ አትጠይቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርህን በወለድ አታበድረው፤ እህልህንም በትርፍ አትስጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርህን በወለድ አታበድረው፤ መኖህንም በትርፍ አትስጠው። |
በሕዝቡ ላይ የሚሆነው እንዲሁ ካህኑ ላይ ይሆናል፤ በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው እንዲሁ በአስተዳዳሪው፥ በአገልጋይቱም የሚሆነው እንዲሁ በእመቤትዋ፥ በሸማቹ ላይ የሚሆነው እንዲሁ በሻጩ፥ በአበዳሪው የሚሆነው እንዲሁ በተበዳሪው፥ በዕዳ አስከፋዩም የሚሆነው እንዲሁ በዕዳ ከፋዩ ይሆናል።
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።
ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።