ዘሌዋውያን 11:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽኮኮ ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽኮኮ ያመሰኳል፤ ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ግን በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽኮኮ ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥንቸል ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ይህ ለእናንተ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽኮኮ ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። |
ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸውም ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እንስሳት መካከል ግመልን፥ ጥንቸልንና ሽኮኮን አትብሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ቢያመሰኩሁም፥ ሰኰናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።