መጽሐፈ ዮዲት 13:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺ ሕዝባችን በመዋረዱ ምክንያት ለነፍስሽ ያልሳሳሽ፥ በአምላካችን ፊትም በቀጥታ መንገድ በመሄድ ጥፋታችንን የተከላከልሽ እግዚአብሔር ለዘለዓለም እንድትከብሪ ያድርግሽ፤ በመልካም ሥራዎችም ይጐብኝሽ።” ሕዝቡም ሁሉ፦ “ይሁን፥ ይሁን” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ይህን ለዘለዓለም እንድትከብሪ ያድርግልሽ፤ ስለ ወገኖችሽ አንቺ ልሙት ብለሽ ወጣሽ እንጂ፥ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔርም ፊት በቀጥታ ሄድሽ እንጂ ለሰውነትሽ አልራራሽምና በቸርነቱ ይመልከትሽ።” ሕዝቡም ሁሉ፥ “አሜን፥ አሜን” አሉ። |