መሳፍንት 6:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በመላው የምናሴ ምድር መልእክተኞቹን ልኮ እንዲከተሉት ጥሪ አደረገ፤ ደግሞም የአሴር፥ የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች ወጥተው እንዲገጥሟቸው መልእክተኛ ላከባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በመላው የምናሴ ምድር መልእክተኞቹን ልኮ እንዲከተሉት ጥሪ አደረገ፤ ደግሞም የአሴር፣ የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች ወጥተው እንዲገጥሟቸው መልእክተኛ ላከባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምናሴን ነገድ ሁሉ መልእክት ልኮ ይከተሉት ዘንድ አስጠራቸው፤ እንዲሁም ወደ አሴር፥ ወደ ዛብሎንና ወደ ንፍታሌም ነገዶች መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ከሌሎቹ ጋር ለመሰለፍ ወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምናሴም ነገድ ሁሉ መልእክተኞችን ላከ፤ እርሱም ከኋላው ሆኖ ጮኸ፤ መልእክተኞችንም ወደ አሴርና ወደ ዛብሎን ወደ ንፍታሌምም ላከ፤ እነርሱም ሊቀበሉአቸው ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምናሴም ነገድ ሁሉ መልክተኞችን ሰደደ እነርሱም ደግሞ ተጠርተው በኋላው ተከተሉት፥ መልክተኞችንም ወደ አሴርና ወደ ዛብሎን ወደ ንፍታሌምም ሰደደ፥ እነርሱም ሊገናኙአቸው ወጡ። |
ዲቦራ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባራቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺህ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤
አሁንም እንግዲህ፦ የፈራ የደነገጠም ከገለዓድ ተራራ ተነሥቶ ይመለስ ብለህ በሕዝቡ ጆሮ አውጅ አለው። ከሕዝቡም ሀያ ሁለት ሺህ ተመለሱ፥ ዐሥርም ሺህ ቀሩ።