መሳፍንት 19:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ምሽት ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር መጥቶ በጊብዓ የሚኖር አንድ መጻተኛ ሽማግሌ ከዕርሻ ሥራው መጣ፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ምሽት ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር መጥቶ በጊብዓ የሚኖር አንድ መጻተኛ ሽማግሌ ከዕርሻ ሥራው መጣ፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ተቀምጠው ሳሉ በእርሻ ቦታ የቀን ሥራውን ፈጽሞ ወደ ቤቱ የሚመለስ አንድ ሽማግሌ በአጠገባቸው አለፈ፤ ይህ ሰው አስቀድሞ ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የመጣ ሲሆን፥ አሁን ግን የሚኖረው በጊብዓ ነበር፤ በዚያ የሚኖሩት ሌሎቹ ሰዎች ግን ከብንያም ነገድ የተወለዱ ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም አንድ ሽማግሌ ከእርሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፤ ይህም ሰው ከተራራማው ከኤፍሬም ሀገር ነበረ፤ በገባዖንም በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፤ የዚያ ሀገር ሰዎች ግን የብንያም ልጆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ አንድ ሽማግሌ ከእርሻው ሥራ ወደ ማታ መጣ፥ ይህም ሰው ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ነበረ በጊብዓም በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፥ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ። |
ከሰማይም በታች የተደረገውን ሁሉ በጥበብ እፈልግና እመረምር ዘንድ ልቤን አተጋሁ፥ ይደክሙባት ዘንድ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣት ከባድ ጥረት ናት።
በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ በዚሁ ጊዜም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር አንድ ሌዋዊ ከይሁዳ ምድር ከቤተልሔም አንዲቱን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት።