መሳፍንት 13:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስቱንም፥ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኑሄም ሚስቱን፣ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማኑሄ ሚስቱን “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጥ እንሞታለን!” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኑሄም ሚስቱን፥ “እግዚአብሔርን አይተናልና ሞትን እንሞታለን” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኑሄም ሚስቱን፦ እግዚአብሔርን አይተናልና ሞት እንሞታለን አላት። |
እርሱም፦ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ማየት ፈርቶ ፊቱን ሸፈነ።
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ፥ ከእናንተ የበረቱትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊታችሁ እንዲያስወጣ፥ እናንተንም እንዲያስገባ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ይሰጣችሁ ዘንድ ነው።