የጌታም መልአክ፥ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለጌታ አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የጌታ መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር።
መሳፍንት 13:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ዳግመኛ ባለመገለጡ፥ ቀደም ሲል የተገለጠላቸው የጌታ መልአክ መሆኑን ማኑሄ ዐወቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ዳግመኛ ባለመገለጡ፣ ቀደም ሲል የተገለጠላቸው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ማኑሄ ዐወቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ዳግመኛ አልተገለጠም ከዚያ በኋላ ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ዐወቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ ዳግመኛ ለማኑሄና ለሚስቱ አልተገለጠም፤ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን ዐወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ ዳግመኛ ላማኑሄና ለሚስቱ አልተገለጠም፥ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። |
የጌታም መልአክ፥ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለጌታ አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የጌታ መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር።