Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 13:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የጌታም መልአክ፥ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለጌታ አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የጌታ መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፣ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን “ምንም አንተ ብታቈየኝ ምግብህን አልበላም፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትፈልግ ግን ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ማኑ​ሄን፥ “አንተ የግድ ብት​ለኝ እህ​ል​ህን አል​በ​ላም፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ብታ​ደ​ርግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ር​በው” አለው። ማኑ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መሆ​ኑን አላ​ወ​ቀም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፦ አንተ የግድ ብትለኝ መብልህን አልበላም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 13:16
5 Referencias Cruzadas  

ቁራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፥ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና።” እነርሱም፦ “እንዳልህ አድርግ” አሉት።


የጌታም መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ዳግመኛ ባለመገለጡ፥ ቀደም ሲል የተገለጠላቸው የጌታ መልአክ መሆኑን ማኑሄ ዐወቀ።


ሚስቱ ግን መልሳ እንዲህ አለችው፥ “ጌታ ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፥ የሚቃጠለውን መሥዋትና የእህል ቁርባኑን ከእጃችን ባልተቀበለን፤ ደግሞም ይህን ነገር ሁሉ ባላሳየንና እንዲህ ያለውንም ነገር በዚህ ጊዜ ባልነገረን ነበር።”


የጌታ መልአክ፥ “ሥጋውን እርሾ ያልገባበትን ቂጣ ወስደህ፥ በዚያ ዐለት ላይ አኑር፤ መረቁንም በሥጋውና በቂጣው ላይ አፍስስ” አለው፤ ጌዴዎንም እንደ ታዘዘው አደረገ።


በዚህ ፍርስራሽ ጉብታ ላይ ለአምላክህ ለጌታ የሚገባውን መሠዊያ ሥራ። ሰባብረህ በጣልኸው የአሼራ ምስል ዐምድ ሁለተኛውን ወይፈን ወስደህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ አቅርበው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos