መሳፍንት 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ሰዎች ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ልጆች ጋር ሆነው በጽፋት ከተማ በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ከተማይቱንም ፈጽሞ ደመሰሷት፤ ስለዚህ ከተማይቱ ሖርማ ተብላ ተጠራች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ሰዎች ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ልጆች ጋራ ሆነው በጻፋት በሚኖሩት ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ከተማዪቱንም ፈጽሞ ደመሰሷት፤ ስለዚህ ከተማዪቱ ሖርማ ተብላ ተጠራች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ ከስምዖን ሕዝብ ጋር በአንድነት ዘምተው በጸፋት ከተማ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ድል አደረጉ፤ ከተማይቱንም ፈጽመው ካጠፉአት በኋላ “ሖርማ” ብለው ሰየሙአት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር ሄደ፤ በሴፌት የተቀመጡትንም ከነዓናውያንን መቱ፤ ፈጽመውም አጠፉአት፤ የከተማዪቱንም ስም ሕርም ብለው ጠሩአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም ከወንድሙ ከስምዖን ጋር ሄደ፥ በጽፋት የተቀመጡትንም ከነዓናውያንን መቱ፥ ፈጽመውም አጠፉአት። የከተማይቱንም ስም ሔርማ ብለው ጠሩአት። |
ጌታም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፥ ከነዓናውያንንም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱንም ከተሞቻቸውንም እርም ብለው አጠፉ፤ የዚያንም ስፍራ ስም ሔርማ ብለው ጠሩት።
ይሁዳም ወንድሙን ስምዖንን፦ “ከነዓናውያንን ለመውጋት ድርሻዬ ወደ ሆነው ምድር አብረን እንውጣ፤ እኔም እንደዚሁ ድርሻህ ወደ ሆነው ምድር አብሬህ እወጣለሁ” አለው። ስለዚህም ከእርሱ ጋር ሄደ።